Русские видео

Сейчас в тренде

Иностранные видео


Скачать с ютуб ኢየሱስ "እኔ ነኝ" ነው (የእግዚአብሔር ልጅ - ክፍል 20) в хорошем качестве

ኢየሱስ "እኔ ነኝ" ነው (የእግዚአብሔር ልጅ - ክፍል 20) 1 год назад


Если кнопки скачивания не загрузились НАЖМИТЕ ЗДЕСЬ или обновите страницу
Если возникают проблемы со скачиванием, пожалуйста напишите в поддержку по адресу внизу страницы.
Спасибо за использование сервиса savevideohd.ru



ኢየሱስ "እኔ ነኝ" ነው (የእግዚአብሔር ልጅ - ክፍል 20)

እግዚአብሔር በሚነድደው ቍጥቋጦ ውስጥ ለሙሴ ተገልጦ ለመጀመሪያ ጊዜ ስሙን ያሳወቀበትን ትራኬ እናስቀድም። ሙሴ፣ “ወደ እስራኤል ሕዝብ ሄጄ ‘የቀድሞ አባቶቻችሁ አምላክ ወደ እናንተ ልኮኛል’ በምላቸው ጊዜ እነርሱ ‘ስሙ ማን ነው?’ ብለው ቢጠይቁኝ ምን እመልስላቸዋለሁ?” የሚል ጥያቄ አቅርቦ ነበር። እግዚአብሔርም፣ “እኔ ‘ያለሁና የምኖር ነኝ፤’ ስለዚህም ‘እኔ ነኝ’ ወደ እናንተ ልኮኛል በላቸው” የሚል ምላሽ ሰጥቶታል (ዘፀ. 3፥13-14፤ አት)። በዚህ ምንባብ ውስጥ “ያለሁ፣ የምኖር፣ እኔ ነኝ” በሚል በሦስት መልኩ የተተረጐመው “ኤህዬህ (אֶהְֽיהֶ)” የሚለው የዕብራይስጥ ቃል ነው። የግሪክኛው ብሉይ ኪዳን (ሰብዓ ሊቃናት) እግዚአብሔር በዚህ ስፍራ ራሱን ያስተዋወቀው “ኤጎ ኤሚ ሆ ኦን” (ἐγώ ειμι ο ων) በማለት እንደ ሆነ ይገልጣል። ይህም በበርካታ የእንግሊዝኛ ትርጕሞች “I AM WHO I AM” ተብሎ ተተርጕሟል። “እኔ ብቻዬን እኔ እንደ ሆንሁ (በግሪክኛው ኤጎ ኤሚ)፣ ከእኔም በቀር አምላክ እንደሌለ እዩ” የሚለው ዘዳግም 32፥39ም ከዚሁ ጋር ይስማማል። ጌታ ኢየሱስ “እኔ ነኝ” ሲል እነዚህን ታሳቢ ያደረገ ስለ መሆኑ ቀጥለን እንመለከታለን።

Comments