Русские видео

Сейчас в тренде

Иностранные видео


Скачать с ютуб ሊቀ ካህናቱ ኢየሱስ (የእግዚአብሔር ልጅ - ክፍል 34) в хорошем качестве

ሊቀ ካህናቱ ኢየሱስ (የእግዚአብሔር ልጅ - ክፍል 34) 3 месяца назад


Если кнопки скачивания не загрузились НАЖМИТЕ ЗДЕСЬ или обновите страницу
Если возникают проблемы со скачиванием, пожалуйста напишите в поддержку по адресу внизу страницы.
Спасибо за использование сервиса savevideohd.ru



ሊቀ ካህናቱ ኢየሱስ (የእግዚአብሔር ልጅ - ክፍል 34)

ክህነት፣ ንግሥና እና ነቢይነት በብሉይ ኪዳኗ እስራኤል ውስጥ በኪዳን ሰጪው እግዚአብሔርና በኪዳኑ ሕዝብ መካከል ያለውን ግንኙነት ሲያበጃጁ ኖረዋል። በዚህም ግንኙነት ውስጥ ሊቀ ካህናቱ፣ ንጉሡ እና ነቢዩ የየራሳቸው ተደጋጋፊ ሚና አላቸው። ከእነዚህ ሦስት አገልግሎቶች መካከል የክህነት አገልግሎትን የተለየ ጉልህ ስፍራ እንዲወስድ የሚያደርገው ሁናቴ ግን ተከስቷል። ከክርስቶስ ልደት በፊት ከ586 ዓመታት ጀምሮ ንጉሣዊው ሥርዐት ከእስራኤል ተመንግሎ ቀረ። ከክርስቶስ ልደት ከ400 ዓመታት አስቀድሞ ደግሞ የነቢያት አገልግሎት እየሟሸሸ መጣ። ከዚያ በኋላ የተጻፉ ሃይማኖታዊ ጽሑፎችም በቅዱሳት መጻሕፍት ዝርዝር ውስጥ አልተካተቱም። ነገር ግን ከባቢሎን ምርኮ መልስ የክህነት አገልግሎት ይበልጥ እየተዋቀረና በአይሁድ ህልውና ውስጥ ማእከላዊውን ስፍራ እየያዘ መጣ። ካህናትም በአይሁድ ኑሮ ውስጥ ቅድሚያ አገኙ። ከዚህም የተነሣ፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር በነበረበት ወቅት የክህነት አገልግሎት በእስራኤል ውስጥ እጅግ በጣም አስፈላጊውና ትልቅ ትኵረት የተቸረው አገልግሎት ነበር፤ በ70 ዓ.ም ኢየሩሳሌምና ቤተ መቅደሱ እስኪፈርሱ ድረስም አልተቋረጠም። ንግሥና፣ ነቢይነትና ሊቀ ክህነት “የክርስቶስ ሥራዎች” ተብለው ይታወቃሉ፤ ሦስቱም ተገልጠውበታልና። የተናገራቸው ቃሎች የነቢይነቱ መግለጫዎች፣ ያደረጋቸው ተአምራት የንግሥናው ጠቋሚዎች፣ በሕይወቱ የከወነው ደግሞ የሊቀ ካህንነቱ ምስክር ናቸው። ሊቀ ካህንነቱ ግን እርሱ ከትንሣኤውም ሆነ ከዕርገቱ በኋላ በሰው-ነት ስለ መገኘቱና አሁንም ስላለው አገልግሎቱ ስለሚያስረዳን በስፋት እንዳስሰዋለን።

Comments