Русские видео

Сейчас в тренде

Иностранные видео


Скачать с ютуб አደራ የሕይወት መንገዴን || Apostolic Songs || Adera Ye Hiwet Menigeden || Apostolic Mezmur || ኦክላንድ መዘምራን в хорошем качестве

አደራ የሕይወት መንገዴን || Apostolic Songs || Adera Ye Hiwet Menigeden || Apostolic Mezmur || ኦክላንድ መዘምራን 1 месяц назад


Если кнопки скачивания не загрузились НАЖМИТЕ ЗДЕСЬ или обновите страницу
Если возникают проблемы со скачиванием, пожалуйста напишите в поддержку по адресу внизу страницы.
Спасибо за использование сервиса savevideohd.ru



አደራ የሕይወት መንገዴን || Apostolic Songs || Adera Ye Hiwet Menigeden || Apostolic Mezmur || ኦክላንድ መዘምራን

ለአንተ ጌታ ኢየሱስ ዘውትር ጠዋት ማታ ክብር ሰጥሃለሁ መልካም ነህ ለሕይወቴ በአንተ ረክቻለሁ አይመስለኝም ነበር ለዚህ የምበቃ አደረክ ኢየሱስ ለአንተ የምተጋ ለአንተ ጌታ ኢየሱስ ለክብርህ ዘምራለሁ ለአንተ ጌታ ኢየሱስ ለክብርህ እሰግዳለሁ ለአንተ ጌታ ኢየሱስ ለክብርህ እልል እላለሁ ለአንተ ጌታ ኢየሱስ ለክብርህ አሸበሽባለሁ በአማልክት ሁሉ ላይ ሥልጣን አለህ በክብር ከፍ ከፍ ያልክ አንድ አምላክ ነህ ከፍ በል /4* ብቻህን በሰማይ ሰማይ ትኖራለህ ፍጥረታትን ሁሉ በኃይል ትገዛለህ ክብር ይገባሃል አንተን አከብራለሁ ታላቅ ነህ ጌታዬ ተመስገን እላለሁ ስላደረክልኝ ስለ ብዙ ውለታህ አይሰለቸኝ ለአንተ ብዘምር በእልልታ ታሪኬን ለውጠህ በአንተ አምሮብኛል ከጉድፍ አንስተህ ለዚህ አብቅተኸኛል ድንቅ ነህ ኢየሱስ ግሩም ስም ይዘሃል ሥልጣን የአንተ ነው ልትከብር ይገባሃል በቃልህ እውነተኛ ታማኝ ለልጆችህ አወቅኩህ ጌታዬ አንተ ብቻህን ነህ አደራ የሕይወት መንገዴን አደራ አደራ የሕይወት መንገዴን አደራ/2* ዘይትህን ሙላው ዘውትር በመቅረዜ በፊትህ ይመርልኝ ጌታ አረማመዴ /2/ ክበርብኝ ኢየሱስ ዘውትር በመንገዴ ሁንልኝ አምላኬ ከፊቴ ሁልጊዜ አንተን ተከትዬ እኔም እንድጓዝ አደራህ ኢየሱስ ከእኔ ጋር ተጓዝ ጥቃቅን ቀበሮን አጥምደህ ያዝልኝ ለሕይወት መንገዴ እንቅፋት እንዳይሆነኝ እንዳላሳዝንህ መንገዴን አደራ ለእኔስ ይሻለኛል መጓዝ ከአንተ ጋራ መንገዴን ለአንተ አደራ እሰጣለሁ በጉዞዬ ሁሉ ተስፋ አደርግሃለሁ አካሄዴ ይመር ዘወትር በፊትህ ይፈጸም በሕይወቴ ኢየሱስ ፈቃድህ እርምጃዬን ሁሉ ለአንተ ክብር ይሁን እንዳሻህ አድርገህ ሥራኝ አደራህን የመንፈስህ ዘይት በሕይወቴ ይብዛልኝ አሳምር ኢየሱስ ዘውትር አካሄዴን ይታደስ ይታደስ ሕይወቴ ፍጠርልኝ ጌታ ንጹህ ልብ ያማረ የተስተካከለ በቃልህ የነጠረ የቀናውን መንፈስ በውስጤ አድስልኝ ሁልጊዜ በሕይወቴ አንተ እንድታየኝ ይታደስ ይታደስ ሕይወቴ ይታደስ ዘይትህ በእኔ ላይ ጌታዬ ሆይ ይፍሰስ ይታደስ ይታደስ ጉልበቴ ይታደስ መንፈስህ በእኔ ላይ ጌታ ኢየሱስ ይፍሰስ የቀደመው ፍቅሬ ለአንተ የነበረኝ ሚያዘምር ሚያናግር የሚያስመሰክረኝ ዛሬም ይንቀሳቀስ ይናገር ክብርህን እንደ ጥንቱ ዘመን ላውጅ ምህረትህን በመንፈስህ እሳት አምላኬ ለውጠኝ ጣፋጩን በረከት አሁንም አብዛልኝ በሕይወቴ ግባ በእኔ ተጠቀም የደረቀው ሕይወቴ በመንፈስህ ይለምልም ለወንድም ለእህቴ የነበረኝ ፍቅር ሕብረት አንድነቴ የሕይወት ትስስር ዳብሮ ከበፊቱ ማየትን እሻለሁ እንደ አሮን ሽቶ እንዲሆን እመኛለሁ መሰራት አለብኝ መታደስ በመንፈስ ጸንቼ እንድቆም እስክትመጣ ድረስ ሕይወቴ በመንፈስ እሳት ተቀጣጥሎ ማራናታ ልበል እንድትመጣ ቶሎ አለኝ ምስጋና ያረክልኝን መቼው አልረሳው ከሕይወቴ ጋራ ቁርኝት አለው በሕይወቴ ላይ ታምር ሰርተኸሃል ምከፍልህ የለም ሁሉ ተችሎሃል አለኝ ምስጋና/2* አለኝ ምስጋና አለኝ ክብር /2* ለአንተ ክብር /2/ ኢየሱስ ጨለማዬ አብርተህልኛል ከሰይጣን እስር አላቀኸኛል ኢየሱስ ለነፍሴ ብዙ ውለሃል ያደረክልኝ ከቁጥር ያልፋል ለክፋት ለኃጥያት ከመገዛት ለሰይጣን ጣኦት ከመሰዋት ለየኸኝ ለአንተ እንዳጥንልህ በሕይወቴ ላይ ድንቅ አድርገህ እጅህ ልትረዳኝ ፈጥና ደርሳለች ነፍሴም ደስ ብሏት ታከብርሃለች በእጥፍ አርገህ ሰላም ሰጠኸኝ በብዙ ደስታ ፍቅርህ በዛልኝ ላመስግነው ዛሬ በመቅደሱ ላመስግነው ዛሬም በመቅደሱ ከፍ ላርገው በአደባባዮቹ ያደረገልኝን ተአምራቱ /2* አወራለሁ ኤልሻዳይነቱ/2* 2 በጠራሁት ጊዜ ኢየሱስ ሰማኝ ከመቅደሱ ሆኖ ተመለከተኝ ከጥፋትም ጉድጓድ ከረግረጉ ጭቃ አወጣኝ አማልኬ ልሆን የክብሩ እቃ ኃይሉን እንዲያስታውቅ ስለ ስሙ አዳነኝ የኤርትራን ባህር ከፍሎ አሻገረኝ በድቅድቅ ጨለማ ብርሃን ሆነልኝ የሰማዩን መና ሕያው ቃል መገበኝ ሕይወቱ ሰውቶ ሕይወትን ሰጥቶኛል በክቡር ደሙ ገዝቶ ልጁ አድርጎኛል ለእኔ ያለውን ፍቅሩን ተረድቼዋለው ላመስግነው ሌላ ምን እከፍለዋለው የእግዚአብሔርን ሥራ በጎነት ያያችሁ ከጨለማው አለም የተላቀቃችሁ ከታላቅ መከራ ጭንቅ ያመለጣችሁ አመስግኑት የእርሱ ምስክሮች ናችሁ በዘመኔ ሁሉ ሐሳብህን በዘመኔ ሁሉ ሐሳብህን ኢየሱስ አገልግዬ ሩጫዬን ጨርሼ መልካሙንም ገድል ተጋድዬ በቅድስናና በፍቅር በቤትህ ውስጥ ኖሬ ማለፍን እሻለሁ ስምህን በምድር ላይ አስከብሬ ስምህን በምድር ላይ አስከብሬ በቅድስና በፍቅር ኖሬ ወደ ወገኖቼ ሳልሰበሰብ ላገልግልህ ኢየሱስ የአንተን ሐሳብ በዘመኔ ሁሉ ሐሳብህን አገለግላለሁ አላማህን መሆኔ ካልቀረ የአንተ ዕቃ መሳሪያ አድርገኝ መገልገያ በዘመኔ ፈቃድህ ይፈጸም በሥራዬ ኢየሱስ አንተ ክበር ዳዊት በዘመኑ ሐሳብህን አገልግሎ አለፈ አላማህን እኔም እንደ ዳዊት ልሁንና ላገልግልህ አንተን በምስጋና ልትጋ መስቀሌንም ተሸክሜ ጸንቼ ልቁም እስከ ፍጻሜ አለሙም ምኞቱም ሁሉ ያልፋሉ ከምድር ጋር አብረው ይጠፋሉ እርዳኝ እኔም ፈቃድህን ልከተል እንድቀበል ከአንተ የጽድቅ አክሊል አይኔ በሚያየው እንዳይረታ እንዳይወድ የዚህን አለም ደስታ ሩጫዬን ጨርሼ እንደ ቃልህ ትግሉ ተጋድዬ ላስደስትህ ቅድስና በሕይወቴ አብቦ በሞገስህ ዙሪያዬ ተከቦ ይሁን ያልከው በሕይወቴ ሆኖ ላይ እሻለሁ ስምህ በእኔ ገኖ ከጥንትም የነበረው በክንዱ ኃይል የሚተማመን እንደ እግዚአብሔር ብርቱ የሚሆን ይነሣ ያውራ እስቲ ይናገር እኔ ነኝ የሚል በሰማይ በምድር የለም ማንም የለም ኢየሱስ ነው ዘላለም/2* ከጥንት የነበረው አምላክህ እግዚአብሔር አንድ ነው በልብህ እንደ ክታብ እሰረው በአይኖችህ መሃል ይሁንልህ እርሱ ብቻውን ነው አምልከው/2* ተስፋን ጨብጦ የተሰለፈ በጠላቱ ፊት በክብር ያለፈ አንድ ነው ይላል ሳይጠራጠር በአምላኩ ወንጌል በቃሉ ሳያፍር እንዴት ምስጉን ነው ጽድቅ የታደለ በእግዚአብሔር ብቻ ጽድቅ ኃይል አለ እርሱን እመነው በአምላክነቱ ልብህ ይቅናለት ለአንድነቱ አንድ መንጋ አለ አንድ እረኛ አንድ ፈራጅ ነው የእውነት ዳኛ መንገድ ሕይወትም ኢየሱስ እሱ ነው ያለ ጥርጥር በእምነት ኃይል አለው እናያለን በእምነት እናያለን የተስፋን ቃል የሰጠው እርሱ የታመነ ነው ፍጹም የማይከዳ የታመነ አምላክ ነው ኢየሱስን ተስፋ አርጎ ያፈረ ሰው የለም ከአፉ ለወጣው ቃል የሚተጋ አምላክ ነው እናያለን በእምነት እናያለን/2* ዛሬ ለእኛ ከብዶ ተራራ የሆነብን ነገ ኢየሱስ ንዶት ሜዳ ሲሆንልን ቅጥሩን አዘልሎ እናያለን ኢየሱስ በምድር ላይ ከብሮ ለአብርሃም እግዚአብሔር ቃል ኪዳን ገባለት ዘርህን አበዛለሁ እንደሰማይ ከዋክብት አብርሃምም አምኖ አምላኩን ጠበቀው እንደ ቃል ኪዳኑ ይስሐቅን ሰጠው ሩት ስትወጣ ብላ ኑአሚን አምላክሽ አምላኬ ሕዝብሽ ሕዝቤ ይሁን ያመለክሺው አምላክ መቼ አሳፈራት የንጉሱ ዳዊት አረጋት ቅድም አያት ሐማ በክፋቱ አይሁድን ለማጥፋት አዋጅ ቢያሳትምም በንጉሥ ቀለበት የአስቴር ልመናዋ ወደ እግዚአብሔር ሲደርስ ሐማ ተዋረደ ሲከብር መርዶክዮስ በእውነት ለሚጠሩት ኢየሱስ ቅርብ ነው ምህረቱ የበዛ ቸር የሆነ አምላክ ነው አምነው ለጠየቁት ለቀረቡትማ ተአምራቱን ሰርቶ ያስደስታል ጌታ ምን ልስጥህ በሞትህ ሞቴን ሻርክ በከፈልከው ዋጋ በፈሰሰው ደምህ ለእኔ ስትወጋ እመላለሳለሁ ያለ ሥጋት ዛሬ በስምህ ጥላ ሥር በዕረፍት አድሬ ምን ልስጥህ ምኔን ላቅርብልህ ኢየሱሴ በምን ላስደስትህ ይህ ነው ምስጋናዬ ይህ ነው አምልኮዬ ይህ ነው ዝማሬዬ ሌላማ ምን አለኝ ጌታዬ /2/ በተዋረደ ልብ ከእግሮችህ ሥር ዛሬም ዝቅ ልበል ልንበረከክልህ ለእኔ እንደዋልክልኝ እንደውለታህ ይገባኛል እኔም ላመሰግንህ ምን ይዤ ልምጣና ኢየሱስ ላስደስትህ ምንድነው ሚያስነሳህ አንተን ከዙፋንህ ምስጋናዬ አርጎ ከአርያም ይድረስ ኢየሱስ ሆይ በፊትህ ዛሬም ነፍሴን ላፍስስ ቃሌ አንተን ይጣፍጥህ ልዘምርልህ ለስምህ የሚገባ ክብር ላመጣልህ አንተን ካስደሰተህ ምስጋና አምልኮዬ ክብር እሰጥሃለሁ እኔ ክብሬን ጥዬ ጻድቃን ሰማዕታት የሚዘምሩባት ጻድቃን ሰማዕታት የሚዘምሩባት/2/ የመላዕክት ዜማ ሁሌ የሚሰማባት/2/ የተስፋ አገሬ ኢየሩሳሌም ናት/2/ ቀን ሌሊት በሐሳቤ ዘውትር የምመኛት/2/ ታላቅና ረጅም ሰፊ ቅጥር ያላት ብርሃኗም በጉ ነው ሁሌ የሚያብራላት የቤቱ መሰረት ሐዋርያት ናቸው በመሰረቷ ላይ ተጽፏል ስማቸው አስራ ሁለት ደጆቿ በእንቁ ተሰርተዋል ክርስቶስ ኢየሱስ መቅደሷ ሆኗታል ፀሐይም ጨረቃም አያስፈልጓትም የእግዚአብሔር ክብር ነው ብርሃን መብራቷ አህዛብ በውስጧ ይመላለሳሉ የምድር ነገስታት ክብርን ያመጣሉ ውሸትና እርኩሰት ፍጹም የለባትም አመፃና ትዕቢት ከቶ አይገባባትም እኔም እነ አብርሃምን ከሩቅ ተመልክቼ ለመድረስ ወሰንኩኝ ከልቤ ጓጉቼ ይህቺ አለም ከንቱ መሆኗን ስላወኩ በአምላኬ እርዳታ እደርሳለሁ ካመንኩ

Comments