Русские видео

Сейчас в тренде

Иностранные видео


Скачать с ютуб አዲስ ነሺዳ ዋሪዳ3 / в хорошем качестве

አዲስ ነሺዳ ዋሪዳ3 / 2 года назад


Если кнопки скачивания не загрузились НАЖМИТЕ ЗДЕСЬ или обновите страницу
Если возникают проблемы со скачиванием, пожалуйста напишите в поддержку по адресу внизу страницы.
Спасибо за использование сервиса savevideohd.ru



አዲስ ነሺዳ ዋሪዳ3 /

።።። ዋሪዳ 3/// ከ ተጨማሪ ግጥሞች ጋር ።።።።። ድንቁርናው፣ ተፍረምርሞ ተበራክቶ ይታይ ነበር፣ የዙልሙ በር ፍትህ ዘግቶ ሳይመጡማ፣ የኛ ፈንታ ኑሩል ዓለም መሸም ነጋ፣ ፅልመት እንጂ ብርሃን የለም ።።። ሺርክን ወደው፣ ለግዑዛን ሲዋከቡ ካለት በላይ፣ ጠጣር ሆነ የሰው ልቡ እንስቲቱን፣ ሲጭኑ አፈር ከነ ነፍሷ አልነበረም፣ ዘብ የሚቆም ሸምጋይ ለርሷ ።።።።። ሳይወለድ፣ የሂዳያው ባለ ተራ በዚያን ጊዜ፣ ኑር ታብቶ ዞላም ደራ ሳናሸልግ፣ የእዝነት ውሃን ስንጠማ በዝነት መጡ፣ አነግበው የዝነት አርማ ።። ባትመጡማ፣ ዘይነል ውጁድ ኸይረል ወራ ግመላቱ፣ ሸክዋው በዝቶ መች ሊያወራ አዝመራውስ፣ መች ሊበቅል መች ሊያፈራ መዲናይቱም፣ አትባልም ሙነወራ ።።።።።። በረቢዑ፣ ብትወልደው አሚነቱ እንደ ምስራቅ፣ ብርሃን ዘራ ላለማቱ ተኳኩሎ፣ ያውም እትብቱ ተቆርጦ ለኛው መጣ፣ መጨረሻ ሁሉን በልጦ ።።።። በዊላዳው፣ ፅልመት ጓዙን ሸካከፈ ስቃይ በደል፣ ከናካቴው ተቀረፈ ባንዲት ንጋት፣ ኑሩን ላለም ያፈገገው የሺ አመቱን፣ የፉርስ ሳት ዶግ አረገው ።።። ባንቱ እኮ ነው፣ ሎሌው ልዑል ሆኖ ያነጋው ነዋይ ተድላው፣ የፈሰሰው የተንጋጋው የታፈርነው ፣ ኢማን ደርሶን የሰለምነው መምሰል ሸሽተን፣ የሐቂቃ ሰው የሆንነው ።።።።። ያላንቱማ፣ ሰዋዊነት እየከሳ በተቆጠርን፣ ከሰው ሳይሆን ከእንስሳ ።። ሊሳን ሃሉ፣ ነቢ ተወለዱ እያለ በደስታ፣ ኩርሲይ ዓርሹ ተማየለ የሂዳያው፣ ጮራ ላለም ብቅ እንዳለ ባንዲት ጀንበር፣ ዙልም ዞላም ኮበለለ ።።።።።። ተወለደ፣ ጌታው ወዶ ያስወደደው እንኳን ዛቱ፣ ስሙ ለአርሽ የከበደው በኑር ማጭድ፣ የሺርክ አረሙን አጨደው የኡሚዩ፣ ሃያል ኢልሙ ጀህሉን ናደው ።።።። ሊነጋጋ፣ ሲል ነውና መጨለሙ በሙስጦፋ፣ ይኸው ነጋልን አለሙ ዋለሉለት፣ ሙላው ቢሻራን የሰሙ በውልደቱ፣ ተፈረጀ ትልሙም ህልሙ ።።።።። ባንቱ እኮ ነው፣ ቢላል ሎሌነት የራቀው የወላጅ ሐቅ፣ ንግስን አልፎ የተላቀው ተደሰቱ፣ ሲል እያዘዘን ሶመዱ ለምን ልዘን፣ በረቢዑ በመውሊዱ ።።።። ሲዲቃችን፣ አቡበክርን ሲድቅ ያጠረው እንደ ዘሀብ፣ የዑመር ልብ የነጠረው ባንቱ ነበር፣ ኡስማን ኑረይን የተቸረው አው ባንቱ ነው፣ ዓሊይ በዒልም የጠጠረው ላንቱ እኮ ነው፣ሰዕድ ላይስት የወጠረው ባንቱ ነበር፣ ሐምዛ ባሰድ የታፈረው ከናካቴው፣ ኻሊድ ሽንፈት ያልሞከረው አርበኛዎ፣ ቃዕቃዕ ሺ ጦር የሰበረው ላንቱ ቢል ነው፣ ሱሃይብ ንግዱ ያልከሰረው ባንቱ ነበር፣ ዙልቢጃደይን የታመረው ጋሻ ጃግሬው፣ ዲራር ዐድው የከወረው ብርሃን ዘልቆ ፣ ፅልመት ደቆ ፍትህ ደምቆ፣ አድሎው ጠልቆ ዙልም ዞላም የመከነው ውዠብርብሩ የሰከነው ኑሩል ዓለም ባንቱ እኮ ነው ኢማን ደርሶን የሰለምነው ጣቃ ተውሂድ የደወርነው ተሺርኩ ዞግ ያገለልነው የወየዘርን የታመርነው የሐቂቃ ሰው የሆንነው ኸይሩል በሸር ባንቱ እኮ ነው የነፍስያን፣ ሰጋር ጋልበው እየጠፉ ሁሉም ንግዱ፣ ኪሳራ ነው በኖ ትርፉ ባትመጡማ፣ ተውሒድ በለው ኢባዳቱ ያላንቱማ፣ መች ሊታወቅ ፆም ሶላቱ ።።።። ጃሂሊያው፣ መቱን ለክፎ ሲነባበር እስልምና፣ እንዳልነበር ሆኖ ነበር ግንስ ድንገት፣ ቀኑ ደረሰና ፍርዱ ተወለዱ፣ ከውኑን አልሚው በተውሒዱ ።።።። ኢማን ደርቆ፣ ሺርኩ ፈልቶ እየናኘ ነቢ ያላንቱ፣ ባሏህ ሚያምን ባልተገኘ ኢማን ደርሶን፣ ጌታን አውቀን የሰለምነው ኑሩል ዐለም፣ ባንቱ እኮ ነው ሰው የሆንነው ።።።።። ትልቁ ሰው፣ መደምደሚያው የሙርሰሉ ሲወለዱ፣ ገደል ገባ ጥል በደሉ ተደሰቱ፣ ሲለን ጎልቶ ቁርአን በርሱ የሚከፋው፣ ብትቆሽሽ ነው ሙዳ ነፍሱ ።።።። ተወለደ፣ ጥረት ልፋቴን ሊያጠፋው ሲል ነው ኢብሊስ፣ በመውሊዱ የሚከፋው ሙሐመድን፣ በረቢዑ ተሰጥቼ ተው አትበለኝ ፣ምኑን ላክብር መውሊድ ትቼ ።።። እንደ ምስራቅ፣ ብርሃን ሚያፈልቀው ውበቱ መልስ ስጪን፣ ውድ እናቱ ወሊይቱ ስትወልጂው፣ ያን የሙላውን የበላይ እንዴት ነበር፣ ገፅታቸው ምድር ሰማይ ።።።።።

Comments