Русские видео

Сейчас в тренде

Иностранные видео


Скачать с ютуб ፊላደልፊያ ክፍል 1 | ሰባቱ አብያተክርስቲያን | ፓስተር አስፋው በቀለ | www.operationezra.com в хорошем качестве

ፊላደልፊያ ክፍል 1 | ሰባቱ አብያተክርስቲያን | ፓስተር አስፋው በቀለ | www.operationezra.com Трансляция закончилась 4 года назад


Если кнопки скачивания не загрузились НАЖМИТЕ ЗДЕСЬ или обновите страницу
Если возникают проблемы со скачиванием, пожалуйста напишите в поддержку по адресу внизу страницы.
Спасибо за использование сервиса savevideohd.ru



ፊላደልፊያ ክፍል 1 | ሰባቱ አብያተክርስቲያን | ፓስተር አስፋው በቀለ | www.operationezra.com

ፊልድልፍያ፡ በስደት የጸናች ቤተ ክርስቲያን (ራእይ 3፡7-13)። የፊልድልፍያ ከተማ በጠንካራ ግንብ የታጠረችና መልካም ኢንዱስትሪ የነበራት ሲሆን፥ ከተማይቱን አቋርጦ የሚያልፍ ጠቃሚ ጎዳና ነበር። ብዙውን ጊዜ ግን የመሬት መንቀጥቀጥ ይነሣባት ነበር። ከዚህም የተነሣ ብዙ ሰዎች ከከተማይቱ ውጭ ይኖሩ ነበር። ይህም የነዋሪዎቿን ቁጥር አመነመነው። ዮሐንስ ይህን መልእክት በሚጽፍበት ጊዜ የፊልድልፍያ ቤተ ክርስቲያን አሁንም ጥቂት ምእመናን ብቻ ነበሯት። ነገር ግን እግዚአብሔር የሕዝብን ብዛት እንደ ዋነኛ በረከት አይቆጥረውም። እርሱን በበለጠ የሚያሳስበው ታማኝነታችን ነው። የፊልድልፍያን ቤተ ክርስቲያን ከደረሰባት ስደት ባሻገር ለክርስቶስ ጸንታ የቆመች ነበረች። በመሆኑም ክርስቶስ ለዚህች ቤተ ክርስቲያን ምንም ዓይነት ተግሣጽ ሊሰነዝር አንመለከትም። ይልቁንም ክርስቶስ ማንም ሊዘጋው የማይችል የአገልግሎት በር እንደሚሰጣቸው ቃል ይገባል። በባለሥልጣናት ፊት የሚከራከሯቸው የማያምኑ አይሁዶች እንኳን ሊዘጉባቸው አይችሉም ነበር። ክርስቶስ አይሁዶችን “የሰይጣን ምኩራብ” ሲል ጠርቷቸዋል። ምክንያቱም የሰይጣን መሣሪያዎች ሆነው በአማኞች ላይ ስደትን ያመጡ ነበር። እንዲያውም፥ ክርስቶስ አንድ ቀን አይሁዶች ክርስቲያኖችን ለማክበር እንደሚገደዱ ይናገራል። ከብዙ አሥርተ ዓመት በኋላ፥ በአንድ ዝነኛ ሰባኪ ወይንም ነቢይ አገልግሎት ይህቺ ቤተ ክርስቲያን በከፍተኛ ደረጃ አደገች። እስልምና የአገሪቱን አካባቢ ከወረረ በኋላ ሳይቀር ይህቺ ቤተ ክርስቲያን ለቀጣይ 500 ዓመታት በክርስቶስ ላይ ያላትን እምነት ለመያዝ በቅታለች። ክርስቶስ በተጨማሪም ለዚህች ቤተ ክርስቲያን “ምድር ላይ የሚኖሩትን ይፈትናቸው ዘንድ በዓለም ሁሉ ላይ ሊመጣ ካለው ከመከራው ሰዓት እጠብቅሃለሁ” የሚል የተስፋ ቃል ሰጥቷል። ክርስቶስ ከፈተናው ሰዓት እጠብቅሃለሁ ሲል ምን ማለቱ እንደሆነ ምሁራን የተለያየ ሐሳብ ያቀርባሉ። በመጀመሪያ፥ እግዚአብሔር ክርስቲያኖች የፈተናውን ሰዓት እንዳይጋፈጡ የሚጠብቃቸው መሆኑን ያሳያል። ሁለተኛ፥ በፈተናው ውስጥ ጉዳት ሳይደርስባቸው እንደሚያልፉ ቃል መግባቱ ነው። ክርስቲያኖች ይህን የተስፋ ቃል በሚተረጉሙበት መንገድ የተለያየ አቋም አላቸው። በመጀመሪያ፥ አንዳንድ አማኞች ክርስቶስ ዮሐንስ ይህን መልእክት ከጻፈ በኋላ በሮም ግዛት ውስጥ በሚገኙ ክርስቲያኖች ሁሉ ላይ ሊመጣ ስላለው የስደት ማዕበል መናገሩ ነው ይላሉ። ክርስቶስ የዚህች ቤተ ክርስቲያን አማኞች በእምነታቸው ምክንያት ከስደቱ እንደሚጠበቁ ቃል መግባቱ ነው ይላሉ። ሁለተኛ፥ ሌሎች ክርስቲያኖች ይህ አማኞች በራእይ 6-19 ውስጥ ለተገለጠው ታላቁ መከራ መፈተን ሳይኖርባቸው ወደ ላይ የሚነጠቁ መሆናቸውን ያመለክታል ይላሉ። ይህ ጥቅስ ብቻ ክርስቲያኖች ከታላቁ መከራ በፊት የሚነጠቁ መሆናቸውን አያረጋግጥም። ክርስቶስ በታማኝነት ጸንቶ ለሚቆም ሰው አያሌ የተስፋ ቃሎችን ሰጥቷቸዋል። ሀ) በአምላኬ መቅደስ አምድ እንዲሆን አደርገዋለሁ። በፊልድልፍያ ብዙውን ጊዜ የመሬት መንቀጥቀጥ ተነሥቶ ካለፈ በኋላ የሚቀሩት የቤተ መቅደስ አምዶች ብቻ ነበሩ። ስለሆነም ክርስቶስ በዘላለማዊ መንግሥቱ ውስጥ ታማኝ ክርስቲያኖች ማንም የማይወስድባቸውና ከቶውንም የማይነቃነቅ የክብር ስፍራ እንዳላቸው ቃል መግባቱ ይሆናል። ወይም ደግሞ አንዳንድ ሀብታም ሰዎች በቤተ መቅደስ አምድ ጨምረው ስማቸውን በዚያው አምድ ላይ ያሰፍሩና ታላቅነታቸውን ያሳዩ ነበሩ። ክርስቶስ ከስደት ሁሉ ባሻገር ለእርሱ ጸንተው የሚኖሩትን በሰማይ የተለየ ክብር እንደሚያገኙ መግለጹ ይሆናል። ለ) ክርስቶስ የአብን፥ የአዲሲቱን ኢየሩሳሌምንና አዲስ ስሙን በግለሰቡ ላይ ይጽፋል። በመንግሥተ ሰማይ ታማኝ ሆኖ የሚጸና በእግዚአብሔር ፊት ይከበራል። የእግዚአብሔርና የኢየሩሳሌም ስም የሚጻፍበት መሆኑ ምናልባትም አማኙ የእግዚአብሔር ልዩ ንብረት ሆኖ የአዲሲቱን ኢየሩሳሌም ዜግነት እንደሚያገኝ የሚያመለክት ይሆናል። አዲሱ ስም አማኙ በመንግሥተ ሰማይ በእግዚአብሔር ፊት የሚኖረውን አዲስ ግንኙነት ሊያመለክት ይችላል። አማኞች በምድር ላይ ሊናቁ ቢችሉም፥ በሰማይ ላይ ግን ታማኞች ሆነው ከተገኙ በእግዚአብሔር ዘንድ ይከብራሉ።

Comments