Русские видео

Сейчас в тренде

Иностранные видео


Скачать с ютуб ፍቺ... መንስኤዎቹና ውጤቶቹ || ነገረ– ፍቺ || ለጎጆዬ || ሚንበር ቲቪ в хорошем качестве

ፍቺ... መንስኤዎቹና ውጤቶቹ || ነገረ– ፍቺ || ለጎጆዬ || ሚንበር ቲቪ 8 месяцев назад


Если кнопки скачивания не загрузились НАЖМИТЕ ЗДЕСЬ или обновите страницу
Если возникают проблемы со скачиванием, пожалуйста напишите в поддержку по адресу внизу страницы.
Спасибо за использование сервиса savevideohd.ru



ፍቺ... መንስኤዎቹና ውጤቶቹ || ነገረ– ፍቺ || ለጎጆዬ || ሚንበር ቲቪ

የጋብቻን ቅዱስነት በማሳየት ተጀምሮ ለጤናማ የትዳር ህይወትና ለስኬታማ የቤተሰብ ምሥረታ እውን መኾን የሚረዱ የተለያዩ ስልትና ዘዴዎችን በማስተዋወቅ ተመልካቾች ዘንድ እየደረሰ የሚገኘው ለጎጆዬ ቤተሰብ ተኮር ፕሮግራማችን፤ ዘወትር ማክሰኞ ምሽት ከ2:30 ጀምሮ በሚንበር ቲቪ ያላንዳች መቋረጥ እየተላለፈ እነሆ ስድስተኛ ወሩ ላይ መድረስ ችሏል። በትዳርና የቤተሰብ ምሥረታ ጉዳዮች ዙሪያ የተሰናዱ በርካታ ኢስላማዊ መፅሃፍትንና ጥናቶችን፣ እንደዚሁም በመስኩ ባለሙያዎች የተፃፉ የምርምር ውጤቶችንና በተለያዩ መነሻ ምክንያቶች የተቀመሩ የጋብቻ አስተማማኝ መረጃዎችን በማጠናቀር በስነ ልቦና ባለሙያው ተወዳጁ ኡስታዝ አብዱልገፋር ሸሪፍ አዘጋጅነት ሲቀርብ በቆየው ለጎጆዬ ፕሮግራማችን በርካታ ርዕሰ ጉዳዮች ተስተናግደውበታል። ለ36 ሰዓታት ወይም ለ 2160 ደቂቃዎች ያህል አየር ላይ በነበረን ቆይታ ከሃገር ቤትና ከባህር ማዶ እጅግ በርካታ ሃሳብና አስተያየቶችን የተቀበልን ሲሆን፤ ስቱዲዮ ድረስ በመምጣት ሲከታተሉን የነበሩ ወደ ሶስት መቶ የሚደርሱ የጎጆዬ ቤተሰቦቻችንም በየፕሮግራሙ ከሚነሳው ርዕሰ ጉዳይ ጋር ትይይዝ ያላቸውን ሃሳብና አስተያየቶች እንደዚሁም ልምድና ተሞክሮዎች በነፃነት ሲያቀብሉን ቆይተዋል። ለዚህም እጅግ የከበረ ምስጋናችንን እናቀርባለን። ዛሬ በአዲስ ምዕራፍ በምንመለከተው "ነገረ– ፍቺ" ርዕሰ ጉዳያችን የፍቺን መንስኤዎችና የሚያስከትላቸውን መልከ ብዙ ውጤቶች ማየት እንጀምራለን። በርዕሰ ጉዳዩ ዙሪያ ልትነግሩን የምትፈልጉት ሃሳብ ካላችሁ በ 0947700070 ላይ ልትደውሉልን ትችላላችሁ።

Comments