Русские видео

Сейчас в тренде

Иностранные видео


Скачать с ютуб ሰው ሙሉ በሙሉ እግዚአብሔርን ይመስላልን? в хорошем качестве

ሰው ሙሉ በሙሉ እግዚአብሔርን ይመስላልን? 3 года назад


Если кнопки скачивания не загрузились НАЖМИТЕ ЗДЕСЬ или обновите страницу
Если возникают проблемы со скачиванием, пожалуйста напишите в поддержку по адресу внизу страницы.
Спасибо за использование сервиса savevideohd.ru



ሰው ሙሉ በሙሉ እግዚአብሔርን ይመስላልን?

በዘፍጥረት 1፥26 ላይ እግዚአብሔር ሰውን በመልኩና በምሳሌው እንደሚፈጥር መናገሩ ሰውን የእግዚአብሔር አቻ ያደርገዋልን? አዲስ ኪዳን ከፈጣሪያችን መልክ ጋር አያይዞ ያለንበትን ሁኔታ እንዴት ይገልጠዋል? ከጌታ ዳግም መምጣት በኋላስ የእግዚአብሔር አቻ የምንሆንበት ሁኔታ ሊኖር ይችላል? በዘፍጥረት 1፥26 ላይ “መልክ” ተብሎ የተተረጐመው የዕብራይስጡ “ጼሌም צֶלֶם” ሲሆን፣ ትርጕሙም ጥላ፣ ሥዕል፣ ምስል ማለት ነው። ይህም ቃል በብሉይ ኪዳን ውስጥ ለ17 ጊዜአት ያህል ጥቅም ላይ ውሏል፤ እነዚህም ዘፍ. 1፥26፡27፤ 5፥3፤ 9፥6፤ ዘኁ. 33፥52፤ 1ሳሙ. 6፥5፡11፤ 2ነገ. 11፥18፤ 2ዜና 23፥17፤ መዝ. 39፥6፤ 73፥20፤ ሕዝ. 7፥20፤ 16፥17፤ 23፥14፤ አሞጽ 5፥26 ናቸው። “ምሳሌ” ተብሎ የተተረጐመው “ዴሙት דּמוּת” የተሰኘ የዕብራይስጥ ቃልም አምሳያ፣ እንደ፣ አርአያ (model)፣ ቅርጽ የሚሉ ትርጓሜዎች አሉት። ይህም ቃል በዕብራይስጡ መጽሐፍ ቅዱስ ጥቅም ላይ የዋለባቸው 25 ስፍራዎች ዘፍ. 1፥26፤ 5፥1፡3፤ 2ነገ. 16፥10፤ 2ዜና 4፥3፤ መዝ. 58፥4፤ ኢሳ. 13፥4፤ 40፥18፤ ሕዝ. 1፥5፡10፡13፡16፡22፡26፡28፤ 8፥2፤ 10፥1፡10፡21፡22፤ ዳን. 10፥16 ናቸው።

Comments